አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ6ኛው የአውሮፓ ኅብረት – አፍሪካ ኅብረት ጉባዔ በቤልጂየም ብራሰልስ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስሎቪኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃኔዝ ጃንሳ ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት መረጃ ለረዥም ጊዜ የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ስለማጠናከር እንዲሁም ስለቴክኒክ እና ኢኮኖሚ ትብብር መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
የአውሮፓ ኅብረት – አፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ዛሬ በብራሰልስ ይጀምራል፡፡
ጉባዔው ዛሬ እና ነገ እንደሚካሄድ እና የሁለቱ ህብረቶች አባል ሀገራት መሪዎች ይካፈሉበታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!