Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብራሰልስ ቆይታቸውን አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቤልጂየም ብራስልስ ቆይታቸውን አጠናቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የአውሮፓ ህብረት እና አፍሪካ ህብረት የጋራ ጉባኤ ለመሳተፍ ነበር ወደ ብራሰልስ ያቀኑት።

ጉባኤው ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በነበረው ቆይታ በሁለቱ ወገኖች ባለው ትብብር ዙሪያ በጥልቀት መክሯል።

የጋራ እና ዘላቂ ብልፅግናን ለማረጋገጥ 150 ቢሊዮን ዩሮ የአፍሪካ-አውሮፓ የኢንቨስትመንት እቅድ ይፋ ተደርጓል።

ይህም የትምህርትና የጤና ዘርፍን ያካተተ ሲሆን፥ የአውሮፓ-አፍሪካ የ2030 የጋራ ራዕይን እና አጀንዳ 2063ን ለማሳካት እንደሚያስችልም ነው የተመለከተው።

በጋራ ጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው በርካታ ሀሳቦች ተቀባይነት ማግኘታቸውን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው የትብብርና የአጋርነት ሁኔታ፣ በሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የአፍሪካ ድምጽ ስለሚሰማበት እንዲሁም የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት መሪ ቃል የተመለከቱ ጉዳዮች ተቀባይነት አግኝቷል።

እንደዚሁም የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነት በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ጉባኤ ላይ አንስታለች።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version