Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 70 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 70 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉም 8 ሺህ 400 የበቆሎ ዱቄት፣ 2 ሺህ ኩንታል አልሚ ምግብ፣ 150 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት እና 56 ሺህ እስር ሳር ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

 

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው እንደገለጹት÷ ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 50 ሚሊየኑ ከባንኩ ሠራተኞች የተሰበሰበ ሲሆን 20 ሚሊየኑ ደግሞ ከናባንኩ የተበረከተ ነው፡፡

ድጋፉም በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ስምንት ዞኖች የሚከፋፈል ይሆናል ተብሏል፡፡

በደጀኑ ጎንፋ

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version