የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 70 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ
ድጋፉም 8 ሺህ 400 የበቆሎ ዱቄት፣ 2 ሺህ ኩንታል አልሚ ምግብ፣ 150 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት እና 56 ሺህ እስር ሳር ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው እንደገለጹት÷ ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 50 ሚሊየኑ ከባንኩ ሠራተኞች የተሰበሰበ ሲሆን 20 ሚሊየኑ ደግሞ ከናባንኩ የተበረከተ ነው፡፡
ድጋፉም በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ስምንት ዞኖች የሚከፋፈል ይሆናል ተብሏል፡፡
በደጀኑ ጎንፋ