Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ15ኛው ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ አሸነፈ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ15ኛው ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል፡፡

ዛሬ ቀን 9 ሰዓት ላይ በጀመረው ጨዋታ የፋሲል ከተማን ሁለት የአሸናፊነት ጎሎች ሽመክት ጉግሳ አስቆጥሯል፡፡ ኦኪኪ ኦፎላቢ እና በረከት ደስታ ቀሪዎቹን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡

በላፉት 4 ጨዋታዎች ደካማ አቋም ያሳየው ፋሲል ከነማ÷ ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ ከሀዋሳ ከተማ ጋር በእኩል 26 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version