አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን “በቶሎ ለመሸጥ” ከእንግሊዝ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰማ።
የእንግሊዝ መንግስት ሮማን አብራሞቪች “ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ግንኙነት አላቸው” በሚል ከቀናት በፊት ክለቡን ለመሸጥ የጀመሩት እንቅስቃሴ ላይ እገዳ ጥሎ ነበር።
ከዚህ ባለፈም በእንግሊዝ በሚያንቀሳቅሱት ማንኛውም ሃብትና ንብረት ላይም የሀገሪቱ መንግስት እገዳ መጣሉ ይታወሳል።
በተጨማሪም የለንደኑ ክለብ በተጫዋቾች ዝውውርና በጨዋታ ትኬት ሽያጭ ላይ እገዳና ገደቦች ተጥለውበታል።
በዛሬው ዕለትም የእንግሊዝ መንግስትና አብራሞቪች የምዕራብ ለንደኑን ክለብ “በቶሎ ለመሸጥ” ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የሽያጩን ሂደት የአሜሪካው ራይን ግሩፕ እንዲጨርስም ነው ስምምነት ላይ የደረሱት።
ከክለቡ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሮማን አብራሞቪች ለቼልሲ ያበደሩትን 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ፓውንድ እንዲሰርዙም በስምምነቱ ተካቷል ነው የተባለው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

