Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብልጽግና ፓርቲ አቶ አደም ፋራህ እና አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ፕሬዚዳንቶች አድርጎ መረጠ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ እያካሄደ ባለው አንደኛ ጉባኤ የፓርቲውን ምክትል ፕሬዚዳንቶች መርጧል።
በዚህ መሰረት አቶ አደም ፋራህን እና አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ፕሬዚዳንቶች አድርጎ መርጧል።
የብልጽግና ትውልድ በአጭር ጊዜ ተወልዶ ወደ ደማቅ ከፍታ እየገሠገሠ ያለና በዚህ ጉባኤ እጅግ የሚገርምና ያደገ ብልጽግናዊ የታየበት ጉባኤ መሆኑን አቶ ደመቀ መኮንን ተናግረዋል፡፡
ይህ ታላቅ ጉባኤ ለሁላችንም ለሰጠን ዕድል በእኔም በኩል እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ነው ያለት፡፡
“የተሰጠንን አደራ እና ኃላፊነት ለመወጣት በዐቢይ ተግባር፣ በደመቀ ጉዞ እና በታላቁ አዳምና አደም መንገድ ለማገልገል፤ አገልጋይነት መሠረቱ መሪነት ነውና ያን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን መናገር እፈልጋለሁ” ብለዋል።
“በግሌ ከኃለፊነት ለመነሳት ፍላጎቱ ቢኖረኝም በዚህ ጊዜ ወደ ጎን ማለት ተገቢ ባለመሆኑ ጉባኤው የሰጠኝን ኃለፊነት ከድሮ በበለጠ ለማገልገል ዝግጁ ነኝ” ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡
“በዚህ ደረጃ 24 ሰዓት እና ሁልጊዜ ሁሉንም ነገሮች ተሸክሞ ከሚሄድ የስራ ባልደረባና የቅርብ አለቃ ጋር መስራት በጣም ጥሩ ነው፤ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ” ብለዋል አቶ ደመቀ በንግግራቸው፡፡
በተመሳሳይ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በጉባዔው የተመረጡት አቶ አደም ፋራህ ባደረጉት ንግግር “ለዚህ ታላቅ ኃላፊነት ስለመረጣችሁን እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡
አያይዘውም “የተሰጠንን ታላቅ አደራ ለመወጣት ሌት ተቀን እንደምንተጋ አረጋግጣለሁ” ነው ያሉት፡፡
ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በሚያደርጉት ጥረትም ጉባዔው አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version