Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
 
በውይይታቸውም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች እና በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
 
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በሀገሪቱ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ልዩ እንክብካቤ እና ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው የቻይና መንግስት በዚህ ረገድ የሚያከናውናቸውን ስራዎች እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።
 
እስካሁን በቻይና ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውንም በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
ፕሬዚዳንት  ፒንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ምክረ ሀሳብ  መሰረት ከቻይና ጋር ያላትን ግኑኝነት እና ሌሎች ልውውጦችን መቀጠል በመቻሏ አድናቆታቸውን ገልፀዋል። 
https://twitter.com/AbiyAhmedAli/status/1232256414002958336
Exit mobile version