አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት አስተዋጽኦ ያበረከቱ የጤና ባለሙያዎችን አመስግነዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በወራራ ይዟቸው የነበሩ አካባቢዎችን ለማስለቀቀ በተካሄደው ዘመቻ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎች የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና እና ግንባር ድረስ በሜሄድ ሙያዊ አበርክቶ ያደረጉ የጤናው ዘርፍ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ÷“በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ወቅት ወደር የለሽ አገልግሎት ሲሰጡ ለቆዩ የጤና ባለሙያዎች ታላቅ ምስጋናዬ ይድረስ”ብለዋል።
“በመጀመሪያ ሰው በመሆናችሁ በሰብዓዊነት የቆሰለውን ሁሉ አክማችኋል፤ ኢትዮጵያዊ በመሆናችሁ ደግሞ ያስተማራችሁን ህዝብና ሀገር በከባድ ጊዜ አገልግላችኋል፤ የጤና ባለሙያ በመሆናችሁ እንዲሁ በጦር ግንባር በመሄድ ሙያዊ ግዴታችሁን ተወጥታችኋል” ሲሉም አመስግነዋል።
“በትምህርትም በከተማም የማይገኙ ብዙ ልምዶችን እንዳገኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ያሳለፋችሁትን ጊዜ በመጻፍ ልምዳችሁን እንድታካፍሉ እጠይቃለሁ” ብለዋል።
የምስጋና እና የእውቅና መርሀ ግብሩን የጤና ሚኒስቴር እና መከላከያ ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል።
በዘመን በየነ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

