አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ ከ7 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት ላይ የተካሄደ የቆላ ስንዴ ልማትን ጎብኙ፡፡
የተጎበኘው የስንዴ ልማት በባላሀብት፣ አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደሮች የለማ ሲሆን፥ ለዚህም መንግሥት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
እንደ ሀገር በተያዘው አቅጣጫ መሰረት የስንዴ ልማትን በስፋት በማልማት ከውጭ የሚገባ ስንዴን በማስቀረት በምግብ ራስን ለመቻል እቅድ ተይዞ በስፋት እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

