አቶ አወል አርባና አቶ አሕመድ ሽዴ በአፋር የቆላ ስንዴ ልማትን ጎበኙ
የተጎበኘው የስንዴ ልማት በባላሀብት፣ አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደሮች የለማ ሲሆን፥ ለዚህም መንግሥት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
እንደ ሀገር በተያዘው አቅጣጫ መሰረት የስንዴ ልማትን በስፋት በማልማት ከውጭ የሚገባ ስንዴን በማስቀረት በምግብ ራስን ለመቻል እቅድ ተይዞ በስፋት እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡