Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢጋድ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ ግጭት ለማቆም መወሰኑን አደነቀ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስትታ ባለሥልጣን (ኢጋድ) የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማሳለጥ ይቻል ዘንድ ግጭት ለማቆም በመወሰኑ አድናቆቱን ገልጿል።

የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚላከውን አቅርቦት ለማሳለጥ እንዲቻል ግጭትን ለማቆም ያስተላለፈው ውሳኔ ተቀባይነት ያለው እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።

ለትግራይ ክልልና ሌሎች በድርቅና በምግብ እጦት ለተጎዱ ክልሎች ሰብዓዊ ዕርዳታ በተጠናከረ መልኩ እንዲደረግ ዓለም አቀፍ አጋሮች የሚቻለውን ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሁሉም ወገኖች ለዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሰላም አማራጮችን ሁሉ እንዲጠቀሙም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ ግጭት ለማቆም መወሰኑን ትናንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version