አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።
ውይይቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል፥ “በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ትሥሥር ታሪካዊ እና ጥልቅ መሠረት ያለው ነው” ብለዋል።
“ከጉርብትና ያለፈ ቤተሰባዊነት ነው። ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና እኔ ነባሩን መሠረት ለሀገሮቻችን የጋራ ብልጽግና መሸጋገሪያ ልናደርገው ቁርጠኞች ነን” ብለዋል በመልዕክታቸው።
የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
ፕሬዚዳንቱ ዛሬ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ የሁለቱ አገራት መሪዎች በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
በውይይታቸው ወቅትም የንግድ፣ የግብርና መዋዕለ ንዋይ ፍሰት፣ የጋራ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ቱሪዝም፣ ኢነርጂ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ባማከለ መልኩ ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።
ሁለቱ መሪዎች በጉብኝቱ ቆይታ በጋራ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን እንደሚቀጥሉ ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

