አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው የበልግ እና መኸር እርሻ 6 ሚሊየን 300 ሺህ ሄክታር በሰብል ለማልማት እየተሠራ መሆኑን የክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
ከዚህ ውስጥም 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታሩ በኩታ ገጠም እንደሚለማ ነው የተመላከተው፡፡
የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ፥ የግብርና ሥራውን ለማሳካት 55 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እና 1 ሚሊየን 10 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ ይከፋፈላል ብለዋል።
በተጨማሪ አርሶ አደሮች በግልና በቡድን የግብርና መካናይዜሽን መጠቀም የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
የፀጥታ ችግር ላለባቸው የወለጋ ዞኖች ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የግብርና ግብአቶች ወደ አካባቢው እየተጓጓዘ መሆኑንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡
ለአርሶ አደሮች ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት ሂደት ላይ ከ8 ዞኖች ለተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በጅማ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በሙክታር ጣሃ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

