Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ዜጎቻቸው ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስተባባሪን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ዜጎቻቸው እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህልና ድርጅት (ዩኔስኮ)፣ የአሜሪካ፣ የአውስትራሊያ እና የኒውዚላንድ አምባሳደሮች ኢትዮጵያን ጎብኙ የሚል ጥሪ ያቀረቡት÷ ዛሬ በላሊበላ ከተማ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን በጎበኙበት ወቅት ነው።
የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር፣ የአሜሪካ አምባሳደር፣ የአውስትራሊያ አምባሳደር፣ የኒውዚላንድ አምባሳደርና ቤተሰቦቻቸው ከቱሪዝም ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ትናንት ወደ ላሊበላ ከተማ ማቅናታቸው ይታወሳል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ለአካባቢው ልማት ድጋፍ የማድረግ፣ በኢምባሲዎቻቸው በኩል የነበሩ የጉዞ ክልከላዎችን የማንሳት እንዲሁም በቀጣይ ለሀገራቸው ዜጎች ኢትዮጵያን እንዲያስተዋውቁ ያለመ መሆኑን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version