Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ።

አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚገኘውን እና በሃገር ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠሪያና የመረጃ ማዕከል ጎብኝተዋል።

በተጨማሪም በኢንስቲትዩቱ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የስልጠና እና መሰል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በለይኩን አለም

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version