አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የጊምቢቹ ወረዳ ነዋሪዎች ከአንድ ዓመት በፊት በአውሮፕለን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የሙት ዓመት መታሰቢያ አደረጉ::
ባለፈው ዓመት መጋቢት 1 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ወደ ናይሮቢ ሲያቀና ቱሉ ፈራ እና ሀማ ቁንጥሽሌ ቀበሌዎች አዋሳኝ ላይ ተከሰክሶ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፋ ይታወሳል::
የአካባቢው ነዎሪዎችም አደጋው ከደረሰ ጊዜ አንስቶ በተለያየ መንገድ ሀዘናቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል::
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ዕምነት መሰረትም ወቅቱን እየጠበቁ የሙት መታሰቢያ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የሙት ዓመት መታሰቢያ አካሂደዋል::
በዘመን በየነ

