Fana: At a Speed of Life!

የጊምቢቹ ወረዳ ነዋሪዎች ከአንድ ዓመት በፊት በአውሮፕለን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የሙት ዓመት መታሰቢያ አደረጉ

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የጊምቢቹ ወረዳ ነዋሪዎች ከአንድ ዓመት በፊት በአውሮፕለን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የሙት ዓመት መታሰቢያ አደረጉ::

ባለፈው ዓመት መጋቢት 1 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ወደ ናይሮቢ ሲያቀና ቱሉ ፈራ እና ሀማ ቁንጥሽሌ ቀበሌዎች አዋሳኝ ላይ ተከሰክሶ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፋ ይታወሳል::

የአካባቢው ነዎሪዎችም አደጋው ከደረሰ ጊዜ አንስቶ በተለያየ መንገድ ሀዘናቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል::

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ዕምነት መሰረትም ወቅቱን እየጠበቁ የሙት መታሰቢያ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የሙት ዓመት መታሰቢያ አካሂደዋል::

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.