Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ከግድያ ሙከራ ተረፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከግድያ መኩራ መትረፋቸው ተገለፀ።

ካርቱም ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ባጀቡት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መፈፁሙን የሀገሪቱ መንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የሀገሪቱ ቴሌቪዥን በዘገባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሁኑ ወቅት ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር አሊ ባክሂት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሸከርካሪ መንገድ ላይ በነበረበት ወቅት ሙከራው እንደተረገበት በመግለፅ፤ ሆኖም ምንም አይነት ጉዳት እንዳላጋጠመ ገልፀዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃመዶክ ወደ ቢሮዋቸው እያቀኑ በነበረበት ወቅት የግድያ ሙከራው እንደተረገባቸው አልጀዚራ ዘግቧል።
 
ሆኖም እስከአሁን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ለተደረገው የግድያ መከራ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።
 
በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የወጡ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የሱዳን ባለስልጣናት የሚጠቀሟቸው ሁለት ነጭ ተሸከርካሪዎች በጎዳና ላይ ቆመው የሚታዩ ሲሆን፥ አንደኛው በመስኮት በኩል ጉዳት አጋጥሞታል ፣ ሌላኛው ተሸከርካሪም በጥቃቱ ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሞት እንደሚታይ ተጠቁሟል።

ምንጭ፡- አረብ ኒውስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version