Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ከሁልሁል ዘመቻ የተመለሰውን የክልሉ ልዩ ኃይል ወደ ድንበር ሸኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በሁልሁል ቀበሌ ሰርጎ የገባውን የአልሸባብ ቡድን ለመደምሰስ የተመለሰውን የክልሉ ልዩ ሃይል ወደ ድንበር ሸኙ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በአፍዴር ዞን ቆህሌ ወረዳ በሁልሁል ንዑስ ቀበሌ ላይ ሰርጎ በገባው አሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ላይ በተደረገው ዘመቻ የተመለሰውን የክልሉ ልዩ ሃይል ነው ወደ ድንበር አሸኛኘት ያደረጉለት።
ከአራት ቀናት በፊት “አቶ” በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ሾልኮ የገባው የአሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን “ሁልሁል” በሚባል ንዑስ ቀበሌ ከተከበበ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ መደምሰሱን የክልሉ መንግስት የፀጥታ ምክር ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።
ለሦስት ቀናት በተካሄደው ዘመቻም ከ100 በላይ የአሸባሪው ቡድን አባላት ሲገደሉ÷ አሸባሪው ቡድን ሲጠቀምባቸው የነበሩ 13 ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው ተገልጿል፡፡
በሽኝት መርሐ ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌን ጨምሮ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሙበሽር ድባድ ራጌ፣ የክልሉ ልዩ ሃይል አመራሮችና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version