Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም እንደገለጹት÷ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥ የተወሰነው÷ የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version