የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም እንደገለጹት÷ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።
የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥ የተወሰነው÷ የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡