አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መግታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጃክ ማ ጋር ተወያዩ።
በአፍሪካ ኖብል ኮሮና (COVID19) ሊያስከትል የሚችለውን የጤና ጉዳት ለመከላከል ቅድመ ዝግጁነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
ዛሬ ጠዋት ከጃክ ማ ጋር በአፍሪካ የCOVID19ን ስርጭት ለመግታት በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መስማማታቸውን ነው ያመለከቱት።
ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ከ10 ሺህ እስከ 20 ሺህ የሚደርሱ ኮሮናን መመርመሪያ ኪቶችን እና 100 ሺህ ማስኮችን ለማሰራጨት ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር በመምረጣቸው ጃክ ማንን አድንቀዋል።
የሚደረገው ድጋፍ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን ለመንከባከብ የሚያስችሉ መመሪያዎችን አካትተው በቅርቡ የተዘጋጁ መጽሐፎችን ይጨምራል።
የCOVID19 ስርጭትን ለመግታት ቁሳዊ ድጋፍን ከዕውቀት ጋር ማጣመር እንደሚያስፈልግም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ያስታወቁት።

