Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመጨረሻው የአፈር ማዳበሪያ በየብስ ትራንስፖርት ተጓጉዞ ተጠናቀቀ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጨረሻው የአፈር ማዳበሪያ በየብስ ትራንስፖርት ተጓጉዞ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ እንዳስታወቀው÷ የአፈር ማዳበሪያ 10ኛ ዙር 500 ሺህ ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ በየብስ ትራንስፖርት ተጓጉዞ ተጠናቋል፡፡

ከጥር ወር ጀምሮ እስካሁን ድረስ 1 ሚሊየን 282 ሺህ 317 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ በድርጅቱ በኩል የተጓጓዘ ሲሆን÷ ይህም በዓመቱ ሊጓጓዝ ከታቀደው 99 ነጥብ 6 በመቶ መሳካቱን ያሳያል ተብሏል፡፡

በግብርና ኮርፖሬሽን የተገዛውን የአፈር ማዳበሪያ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት÷ ከሞሮኮ፣ ከዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ እና ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ አጓጉዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version