Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኡጋንዳ የልዑካን ቡድን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም ፣የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌ/ጄ ሙሆዚ ኪኑሩጋባን ጨምሮ ሌሎች የደህንነትና ወታደራዊ አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡

ለልዑካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና እና ከፍተኛ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል፡፡

ቡድኑ በነበረው ቆይታ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ኢንስቲትዩቱ እያካሄደ ስለሚገኘው ዘርፈ ብዙ ክንውኖች በዋና ዳይሬክተሩ አማካኝነት ገለጻ እንደተደረገለት ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

በተመሳሳይ ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የስራ ጉብኝት አድርጓል።
በዚሁ ወቅት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል÷የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከልና የወንጀል ምርመራ ሥራ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ መተግበሩን ገልፀዋል።
የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦርየም በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በሀገሪቱ የሕብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እያከናወነ ላለው መልካም ስራ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
ልዑካን ቡድኑ በቀጣይ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በፖሊሳዊ አገልግሎት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርግ መገለጹን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
103,188
People reached
5,703
Engagements
Boost post
961
13 Comments
17 Shares
Like
Comment
Share

 

Exit mobile version