የኡጋንዳ የልዑካን ቡድን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም ፣የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌ/ጄ ሙሆዚ ኪኑሩጋባን ጨምሮ ሌሎች የደህንነትና ወታደራዊ አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡
ለልዑካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና እና ከፍተኛ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል፡፡
ቡድኑ በነበረው ቆይታ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ኢንስቲትዩቱ እያካሄደ ስለሚገኘው ዘርፈ ብዙ ክንውኖች በዋና ዳይሬክተሩ አማካኝነት ገለጻ እንደተደረገለት ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡



