Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አየር ኃይሉ ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር በላቀ ዝግጁነት ላይ ነው – ሌ/ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አየር ኃይሉ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ፡፡

የኢፌዲሪ አየር ኃይል አካዳሚ በኤሌክትሮኒክስ፣ በአውሮፕላን አካል እና ሞተር ጥገና እንዲሁም በመሰረታዊ የአቪየሽን ሙያ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።

ሌ/ጀኔራል ይልማ መርዳሳ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ አየር ኃይሉ ከሀገራዊ ለውጡና ከተቋማዊ ሪፎርሙ በኋላ የዝግጁነት አቅሙን ለማሳዳግ በሰው ኃይል ግንባታ፣ በዘመናዊ ትጥቆች እና ቴክኖሎጂ ብሎም ሰፋፊ የውጊያ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በትኩረት መስራት መቻሉን ገልፀዋል።

“ተመራቂዎች ያለንበትን ወቅት በመረዳትና የተማራችሁትን ሙያ ወደ ተግባር በመቀየር ሀገራዊ ግዴታችሁን መወጣት አለባችሁ” ሲሉ ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ለታላቅ ሀገር ታላቅ ተቋም በመገንባት ብሎም ብቃትና ጥራት ያላቸውን ባለሙያዎችን በማፍራትና የኢትዮጵያን ጠላቶች ድባቅ በመምታት አየር ኃይሉ የጀግኖች መፍለቂያ መሆኑን በተግባር እያስመሰከረ እንደሚገኝም ዋና አዛዡ ተናግረዋል።

Exit mobile version