Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአልጄሪያ ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ታቡን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ታቡን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አልጀርስ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ሲደርሱም በፕሬዚዳንቱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ግንኙነት ላይ መምከራቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ውይይቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ተቡን ጋር በነበራቸው ቆይታ ደስተኛ መሆናቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያና አልጄሪያ ያላቸው ታሪካዊ ግንኙነት ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ መሆኑንና ሀገራቱ ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ የሚችልባቸው በርካታ ዘርፎች እንዳሉም ጠቁመዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version