Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ እያከናወነ ያለው ስራ የሚመሰገን መሆኑን ገለፁ

 አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ እያከናወነ ያለው ስራ የሚመሰገን መሆኑን ገለፁ።
 
የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ ጉባኤ ዛሬ ተካሂዷል።
በጉባኤው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፥ የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ እስካሁን ላደረገው ጥረት አመስግነው፥ ጥረቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
ሴቶች የችግሩ ሰለባዎች ብቻ ሳይሆኑ የመፍትሄ አካል ሊሆኑ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ሰላም የህልውና ዋስትና የእድገት መሰረት መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ዜጋ በሀገሪቱ ሰላምን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች ስኬታማ እንዲሆኑ የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የሰላም እጦትና የግጭት መበራከት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚጎዳ ቢሆንም የችግሩ ዋነኛ ገፈት ቀማሽ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ፀረ-ሰላም ኃይሎች በንጹሃን ወገኖች ላይ እየፈጸሙት ያለውንም ድርጊት አውግዘዋል፡፡
የሕዝቡን ሰላም ለማወክና የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ አካላት ከተያያዙት የጥፋት መንገድ ተመልሰው የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ እና ችግሮችን በውይይት እንዲፈቱም ጠይቀዋል፡፡
የሰላም ጥረቱ ስኬታማ እንዲሆን ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንደሚያደርግም መግለጻቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግና
Exit mobile version