Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከተማ አስተዳደሩ 200 ሺህ ሊትር ሳኒታይዘርና ሳሙና ወደ ከነማ የመድሃኒት መደብሮች እያስገባ ነው

አዲስ አበባ፣መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተፈጠረውን የእጅ ንጽህና መጠበቂያ እጥረት ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ 200 ሺህ ሊትር ሳኒታይዘር እና ሳሙና በዛሬው እለት ወደ ከነማ የመድሃኒት መደብሮች በማስገባት ላይ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ የቅድመ መከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል።
 
በዚህ መሰረትም በዛሬው ዕለት በሀገር ውስጥ የተመረተ 200 ሺህ ሊትር የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በከተማዋ ወደሚገኙ የከነማ ፋርማሲዎች በማስገባት ላይ ይግኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመሆን የንጽህና መጠበቂያዎቹን ወደ ከነማ የመድሃኒት መደብር የማስገባት ስራ ላይ ተሳትፈዋል።

ህብረተሰቡ ከነገ ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ በሁሉም የከነማ መድሃኒት መደብሮች በመገኘት አንድ ሊትር ሳኒታይዘር በ80 ብር እንዲሁም 250 ሚሊ ሊትሩን ደግሞ በ40 ብር መግዛት እንደሚችሉ የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

መግዛት ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ የልየታ ስራ በመስራት የከተማ አስተዳደሩ ሳኒታይዘሮቹን ለተጠቃሚዎች በነጻ የሚያቀርብ መሆኑንም ገልጿል።

Exit mobile version