Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።

ፕሬዚዳንቷ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በንግስቷ ህልፈት በኢትዮጵያ ህዝብ እና በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

ንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ በትናንትናው እለት በ96 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

Exit mobile version