Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለስራ ጉብኝት ጂቡቲ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለስራ ጉብኝት ጂቡቲ ገብተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጂቡቲ አብሮ መግባቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ጂቡቲ ሲደርሱም የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Exit mobile version