አዲስ አበባ ፣ መስከረም 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ስርአቶች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በትናንትናው ዕለት የመስቀል ደመራ በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሥነ ስርአት መከበሩ ይታወሳል።
በተለይም በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፀዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ምዕመናን እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት ነው በድምቀት የተከበረው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

