Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሶስተኛው ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ሶስተኛው ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1 ቀን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የህብረተሰቡን እና የተቋማትን ንቃተ ህሊና በማጎልበት እራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል በሚያስችሉ መርሐግብሮች ሊካሄድ ነው።

 

ሁነቱ የኢንፎርሜሽንና ደህንነት የማረጋገጥ ስራን ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ ለማድረግ እንዲያስችል ያለመ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ገልጸዋል ።

 

ሶስተኛው ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ወር “የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ለሃገር ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው፡፡

 

የዲጂታል ማህበረሰብ ለመገንባት በተያዘው እቅድ ውስጥ የሳይበር ደህንነት ሚናው ከፍ ያለ እንደመሆኑ ከዚህ አንፃር እቅዱን የሚመጥን ስትራቴጂ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት እየተነደፈ መሆኑ ታውቋል ።

 

በዚህ ረገድ የሀገርን የዲጂታል ሉአላዊነት ለመጠበቅም አቅም ግንባታ ላይ በስፋት እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

 

በሳይበር ደህንነት ወሩ በግሉ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማትን ተሳትፎ በማሳደግ የሀገርን የሳይበር ደህንነት የማረጋገጥ ስራው የተቀናጀ እንደሚደረግም ተመላክቷል።

 

በሜሮን ሙሉጌታ

Exit mobile version