Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ጋር ተወያዩ።

አቶ ደመቀ ከልዩ መልዕክተኛው ማይክ ሐመር ጋር ባደረጉት ውይይት መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ልዩ መልዕክተኛው በበኩላቸው አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለሚካሄደው የሰላም ውይይት ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

በውይይታቸው ረጅም ዘመን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

 

Exit mobile version