አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ ሙሉጌታ መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት÷ እንግዶቹ የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኩ አንድ አካል የሆነው ካርቢኮ ኢትዮጵያ የተሰኘው የጣሊያን ኩባንያ የማስፋፊያ ሥራዎች መጎብኘቱንም ተናግረዋል፡፡
በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተመረቱ ያሉ የሱፍ ልብሶች፣ የሴቶች የእጅ ቦርሳ፣ ካልሲና ሌሎች የስፖርት አልባሳት ለውጭ ገበያ እየቀረቡ መሆኑ ተመላክቷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

