Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱ የኢትዮጵያን የዲጅታል ስኬት ለማሳየት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶኒዮ ፔድሮ ጋር በኒጀር ኒያሚ ተወያይተዋል፡፡
 
አንቶኒዮ ፔድሮ የዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ በፈረንጆቹ ሕዳር 28 ቀን 2022 በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል።
 
መድረኩ የኢትዮጵያን የዲጅታል ስኬት ለሌሎች ለማሳየት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ጠቁመው÷ በከፍተኛ ደረጃ እንድትወከልም ጠይቀዋል።
 
አቶ ደመቀ መኮንን ስለግብዣው አመስግነው መንግስት የመድረኩን መካሄድ እንደሚያግዝ ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
 
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version