Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን ወክለው ላገለገሉ አምባሳደሮች ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ኢትዮጵያን ወክለው ሲያገለግሉ ለቆዩ አምባሳደሮች ምስጋና አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ “ሀገርን ማገልገል ዕድል፣ ተልዕኮን መፈጸም ደግሞ ድል ነው” ብለዋል።

“የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁ አምባሳደሮቻችንን ኢትዮጵያ ታመሰግናቸዋለች” ሲሉም ገልጸዋል።

አምባሳደሮቹ በዓለም መድረክ ላይ ሳይቆጠቡ ላሳዩት ውክልና ምስጋናዬን አቀርባለሁም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

Exit mobile version