Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሸገር ከተማ ይፋዊ ምስረታን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ የፓናል ውይይት እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸገር ከተማ ምስረታን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ የፓናል ውይይት እየተካሔደ ነው፡፡

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ፣ የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡

የሸገር ከተማ ይፋዊ ምስረታ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፥ ለዚህ የሚረዱ የተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተካሔዱ ይገኛሉ፡፡

በፓናል ውይይቱ በከተማዋ ምስረታ ላይ ያተኮሩ ሁለት ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።

በለሊሴ ተስፋዬ እና ዳግማዊ ዴክሲሳ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version