Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች  መንግሥት 15 ቶን የሚመዝን የኮቪድ-19 መከላከያ ግብዓት  ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች  መንግሥት 15 ቶን የሚመዝን የኮቪድ-19 መከላከያ ግብዓት  ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገች።

የተላኩት ግብአቶች የንክኪ መከላከያ ልብሶችንና የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን ያካተተ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች  መንግሥት እርዳታ ምስጋና አቅርበዋል።

ለሀገሪቱ ኤሚር ሼህ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከአህጉሪቷ ጋር በአጋርነት በመቆማቸው  አደንቃለሁ ብለዋል።

Exit mobile version