አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከለውጡ ወዲህ ለተከናወኑ ተግባራት ሰልፍ በመውጣት ድጋፍ ላቀረቡ ወገኖች ምስጋና አቀረቡ፡፡
አቶ ሽመልስ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ሁሉን አቀፍ ብልጽግና እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡
ነጻነት፣ እኩልነት እና ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት የኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሁሉም አካባቢዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል፡፡
የሰልፉ ተሳታፊዎችም ለነጻነት፣ እኩልነትና ፍትሕ ለተካሄደው ትግል እንዲሁም ከለውጡ በኋላ ለተመዘገቡት ድሎች እና ስኬቶች እውቅና ሰጥተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!