አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለቀድሞው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ ምስጋና አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዋና ዳይሬክተሩ በሃላፊነት ጊዜያቸው ላበረከቱት መልካም አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይ የሕይወት ምዕራፋቸውም መልካም ነገር እንዲገጥማቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡