Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጉባ ኮርስ እና የድህረ ምረቃ ዕጩ መኮንኖችን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ በሁርሶ ሰላም ማስከበር ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ የጉባ ኮርስ እና የድህረ ምረቃ ዕጩ መኮንኖችን አስመረቁ።

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ  በሁርሶ ማሰልጠኛ  ያሰለጠናቸው እጩ መኮንኖች ዘመኑ የሚጠይቀውን ወታደራዊ ሳይንስ እና የአመራር ጥበብ የተካኑ መሆናቸው ተገልጿል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ጀኔራል መኮንኖች፣ የቀድሞ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Exit mobile version