Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የስሎቫንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስሎቫንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታንጃ ፋጆን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
 
ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 
የስሎቫንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
በውይይታቸው በተለይም የሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ።
Exit mobile version