Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ ወግ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመደመር ትውልድ መጽሐፍን መነሻ ያደረገ “የመደመር ትውልድን መቅረፅ” በሚል ርዕስ የአዲስ ወግ ውይይት ተካሂዷል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የሚዘጋጀው አዲስ ወግ ውይይት ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል።

ዛሬም “የመደመር ትውልድን መቅረፅ” በሚል ርእስ ላይ በወዳጅነት አደባባይ ውይይት ተካሂዷል።

ለውይይቱ መነሻ ሀሳብ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፈሰር) ያቀረቡ ሲሆን፥ “ምን አይነት ባህሪ ያለው ትውልድ ቢኖር ሀገር ወደ ምንፈልጋት ልትሄድ ትችላለች?”ሲሉ በፅሁፋቸው ጠይቀዋል።

መሰል ተቀራርቦ መነጋገሩም ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሀገሩን የሚወድ ማህበረሰብ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስም ይህም ዝም ብሎ በስሜት የሚመራ ሳይሆን ለህብረተሰቡ ማሰብ የሚችል መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

ትውልድን ለመቅረጽ ቤተሰብ ፣ የማህበረሰብ ተቋማት እና ት/ቤቶች የእውቀት ፍላጎትን በመፍጠር ፣ ክህሎትን በማዳበር እና አብሮ መኖር እንዴት እንደሚቻል በማስተማር ሠላማዊ ትውልድ መፍጠር የሁሉም ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ፓኖስ ሀዘንድሪያስ (ፕሮፌሰር) በበኩላቸው÷ በትምህርት ስርዓታችን ተማሪዎች ውስጣቸው ያሉትን ክህሎት በማውጣት እራሳቸውን መሆን እንዲችሉ የሰዋዊ ክህሎታቸውን እና የሀገር በቀል እውቀትን ማሳደግ ላይ ማትኮር ይበባል ብለዋል፡፡

አዲሱን የመደመር ትውልድ ለመቅረጽ በሚደረገው እንቅስቃሴ አሁን ሀገራችን ያለችበትን አውድ በመረዳት የአሁኑ ትውልድ የገባበትን መቋሰል በማከም ቤተሰብ እና የት/ት ተቋማት ላይ መተኮር እንደለበትም በውይይቱ ተነስቷል፡፡

የመደመር ትውልድን ለመቅረጽ የት/ት ስርዓቱን ማሻሻል፣ የመምህራን አቅምና ስነምግባር ማሻሻል፣ የትውልዱን የንባብ ባህል ማሳደግ እና የምን አገባኝ ስሜትን የማጥፋት ስራ ከቤተሰብ ጀምሮ መሰራት እንዳለበትም ነው በውይይቱ ተሳታፊዎች የተነሳው፡፡

የመደመር ትውልድን መፍጠር ላይ እየተደረገ ባለው ውይይት ተጋባዥ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

በታሪኩ ለገሰ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version