አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀገር አቀፍ ደረጃ በ5ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከሚተከለው ውስጥ 45 በመቶው ለደን የሚውል ሲሆን ቀሪው 55 በመቶ ደግሞ ለጥምር ግብርና እና ፍራፍሬ ልማት ይውላል ተብሏል፡፡
የዐረንጓዴ ዐሻራ መርሐ- ግብር ለአካባቢ ጥበቃ እና ለተፈጥሮ ሐብት ልማት መፍትሄ ከመሆን ባሻገር የምግብ ዋስትን ለማረጋገጥ ያግዛልም ነው የተባለው።
በአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማዳረስ መቻሉም ተገልጿል።
ቀደም ሲል የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የተሠሩ ሥራዎች በአሁኑ ሰዓት ጥገና እንዳስፈለጋቸው እና በዚሁ መሠረት 1 ሚሊየን ሄክታር ያህሉ የመስኖ ልማት ሥራ ጥገናና ዕድሳት እንደተደረገለት ነው የተገለጸው።
ተዳፋት የሆኑና የተራቆቱ አካባቢዎችን ከንክኪ ነፃ በማድረግ መልሶ ለማልማት በተያዘው ዕቅድ 800 ሺሕ ሄክታር መሬት መሸፈን መቻሉም ተጠቁሟል፡፡
መርሐ-ግብሩ ሕዝብ አሳታፊ መሆኑም ተጠቁሞ ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ማኅበራት በባለቤትነት መሠጠቱ ተመልክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

