አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሶማሊያውን ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

