Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሠሩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በሱዳን ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሠሩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉዳዩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ሕዝቦች ብዙ ፈተናዎችን እየተጋፈጡ በሚገኙበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የሐሰት ውንጀላዎችን በማሰራጨት የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማሳካት የሚጥሩ ወገኖች እንዳሉ ጠቁመዋል።

እነዚህ አካላት ኢትዮጵያ በሱዳን ድንበር አካባቢ ወታደሮቿን አስጠግታለች የሚል የሃሰት መረጃ እያሰራጩ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

ይህን የወንድማማች ሀገራትን ግንኙነት የሚያሻክር የሃሰት ውንጀላም ኢትዮጵያ በጽኑ እንደምታወግዘው አስገንዝበዋል፡፡

 

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ያለው ጉዳይም በውይይት እንደሚፈታ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version