አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012( ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኮቪድ-19 ህመምተኞች እንዲሆን በሚሌኒየም አዳራሽ የተዘጋጀውን የህክምና ማዕከል ጎበኙ።
ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ህክምና የሚያገኙበት ማዕከል ይሆናል ነው የተባለው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው 1 ሺህ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን እንዲይዝ ተደርጎ እየተዘጋጀ ያለውን ማዕከል ተዘዋውረው በመጎብኘት የተከናወነውን ስራ ገምግመዋል።
ሚሌኒየም አዳራሽ ለድንገተኛ ወረርሽኝ ምለሽ መስጠት በሚችል ትልቅ ሆስፒታል ደረጃ መዘጋጀቱም ተገልጿል ።
በአሁኑ ወቅት 360 አልጋዎች ዝግጀቱ ሆነዋል፤ ቀሪዎቹም አልጋዎች በሳምንት ውስጥ ዝግጁ እንደሚሆኑም ነው የተመለከተው።
በህክምና ማዕከሉ 40 የፅኑ ህክምና መስጫ አልጋዎች እና 60 የማገገሚያ አልጋዎችም የኖሩታል።
የህክምና ማዕከሉ 700 የህክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺህ ሰራተኞች እንደሚኖሩትም ነው የተገለፀው።
በአልአዛር ታደለ

