አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 108 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው የ667 ላቦራቶሪ ምርመራ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 108 መድረሱን ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው አንድ የ62 ዓመት ሴት ሲሆን ከአሜሪካ መጠው በለይቶ ማቆያ የነበሩ ናቸው ፣ ሌላው የ19 ዓመት ወጣት ከሳዑዲ አረቢያ መጥቶ በለይቶ ማቆየ የነበረ ሲሆን ሶስተኛ የ52 ዓመት ሴት ደግሞ እየተጣራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
በኢትዮጵያ እስከአሁን 7 ሺህ 557 ሰዎች የላብራቶር ምርመራ ተደርጎላቸው በ108 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
እንዲሁም 16 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን አንድ ሰው ደግሞ በጽኑ ህሙማን ህክምና መስጫ ይገኛል ተብሏል።

